ኮቪድ-19 (አዲስ ኮሮናቫይረስ) - መረጃ፤ አገልግሎት፤ አና ንብረት የዋሽንግተን ስቴት

ከቤት መውጣት እና COVID-19 ክትባት መፈለግ አይቻልም? 

ለመመዝገብ ሶስት መንገዶች አሉ

የ COVID-19 የስልክ መስመር፦ ለሠራተኞች ፣ ለንግድ ሥራዎች ፣ ለክትባት ቀጠሮዎች እንዲሁም ለሌሎችም የሚሰጥ እገዛ 

ስል COVID-19 ጥያቄዎች ካልዎት ወይም የክትባት ቀጠሮን ለማስያዝ እገዛ ከፈለጉ, እባክዎን ለ 1-800-525-0127 በመደወል የ# ምልክቱን ይጫኑ። እነሱ መልስ ሲሰጡ, የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለማግኘት የቋንቋዎን ስም ይጥሩ። የስልክ መስመሩ በየቀኑ ክፍት ነው እንዲሁም ሰዓቶቹ በ Department of Health ዌብሳይት ላይ (በእንግሊዝኛ ብቻ) ተዘርዝረዋል። 

የንግድ ሥራ ጥሰቶችን ሪፖርት ያድርጉ

የንግድ ድርጂቶች ለሠራተኞች እና ለደንበኞች ተገቢ የሆነ የጤና እና የደህንነት እርምጃዎችን መተግብር ይጠበቅባቸዋል። ጥሰቶችን ሪፖርት ማድረግ ከፈልጉ, በራስዎ ቋንቋ እገዛ ለማግኘት፣ እባክዎን ከላይ በተጠቀሰው የ COVID-19 የጥሪ መስመር ይደውሉ። የሆነ ሰው ሰለ ጥሰቱ ጥያቄዎችን ጠይቆ እርስዎን በመወከል ቅሬታዎችን ሊጠይቅዎት ይችላል። ቅሬታዎን ለማስገባት ፣ ስምዎን ወይም የእውቂያ አድራሻዎን ማጋራት አይጠበቅብዎትም።

እንዲሁም ቅሬታዎን በ እንግሊዘኛ ቋንቋ በ የ COVID-19 ጥሰቶችን ሪፖርት ያድርጉ ገጽ ላይ ማስገባት ይችላሉ

የእርስዎን ስም ወይም የእውቂያ መረጃ ካቀረቡ ፣ አንድ ሰው ለዚህ መረጃ ይፋዊ የመዝገብ ጥያቄ ካቀረበ መረጃው ለዛ ሰው በይፋ ሊገለጽ እንደሚችል እባክዎን ልብ ይበሉ። በ የገዢው የግላዊነት ማስታወቂያ ውስጥ በ (እንግሊዘኛ ብቻ) የተገለጹት ማስታወቂያዎች በመንግስት የሕዝብ መዝገቦች ፣ RCW 42.56 ስር በተዋቀረው ሕግ በተፈለገበት ጊዜ ይለቀቃል

ለሥራተኞች፣ ለንግድ ሥራዎች እና ለድርጂቶች የሚሰጡ ተጨማሪ እገዛዎች

የትርጉም ሥራ አገልግሎቶችን በመጠቀም ፣ የጥሪ መስመሩ ወደ አጠቃላይ መመሪያዎች እና ሃብቶች ሊመራዎት ይችላል። አሁንም ድረስ ጥያቄ ካልዎት የ COVID-19 የንግድ ሥራ እና የሰራተኞች ጥያቄዎችን ቅጽ በመሙላት ሊያግዝዎት ይችላሉ። መልስዎችን ለማግኘት እንዲረዳዎ የእውቂያ መረጃዎን ይጠየቃሉ።

የኮሮናቫይረስ (COVID-19) ክትባት

ስለ  COVID-19 ክትባቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የ COVID-19 የክትባት ገፃችንን.

  WA Notify የስማርት ስልክ መተግበሪያ ማስታወቂያዎችን ያሳያል
  ስለ WA Notify የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ፣ ስልክዎ ላይ እንዴት እንደሚያክሉ ማወቅን ጨምሮ፣ WANotify.org ን ይጎብኙ።
  ከ ንብረት ጋር የተያያዙ የሰራ ቅጥሮች እና ንግዶች

  የስራ አጥ ጥቅማጥቅም

  ሥራዎን ካጡ, ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለሥራ አጥነት ክፍያ ጥያቄ እንዴት እንደሚሞሉ መረጃ ከፈለጉ ፣ ወደ 1-800-318-6022 ይደውሉ፡፡ ምላሽ ሲይገኙ፣ ቋንቋዎን በመንገር የ ትርጉም አገልግሎት ያግኙ፡፡

  ሰራተኛና አሰሪ

  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በእኛ ግዛት ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን እና አሰሪዎችን ይነካል፡፡

  የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ, ሰራተኞች ማድረግ ያለባቸው ነገሮች፡

  • ሰራተኞችን ስለ ኮቪድ-19 ምልክቶች በሚገባቸው ቋንቋ ማስተማር፡፡
  • የሰውነት መራራቀን ማጎልበት፡፡
  • ተከታታይ ን ህና መጠበቅ፡፡
  • በተደጋጋሚ እጅን በደንብ መታጠብ፡፡
  • የታመሙ ሰራተኞች በቤት እንዲቆዩ ማድረግ፡፡

  ስለ የተከፈለ የህመም ፈቃድ፣ የሰራተኞች ካሳ እና የስራ ቦታ ደህንነት መስፈርቶች ማጠቃለያ በተመለከተ ለተለመዱ ጥያቄዎች መልሶች Department of Labor & Industries (ከሰራተኛ እና ኢንዱስትሪዎች ክፍል) በብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ።

  ስለ ስራ ቦታዎ ደህንነት ስጋት ካሎት, ቅሬታዎን ለስራተኛ እና ኢንደስትሪ በዚህ ስልክ ቁጥር 800-423-7233 ያሳውቁ፡፡ የ ስልክ ትርጉም አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፡፡

  ሰለ ንግዶ እና ሰራተኞች ማንኛውም ጥያቄ ካሎት በዚህ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ, የሰራተኞች ደህንነት ዲፓርትመንትን በ 855-829-9243 በመደወል ያሳውቁ፡፡

  የጤና ጥበቃና የጤና ኢንሹራንስ

  ነጻ ወይንም በትንሽ ክፍያ የህክምና አገልግሎት መስጠት፡፡ የ ህክምና አገልግሎት ለማግኘት በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-855-923-4633፡፡ ምላሽ ሲያገኙ, ቃንቅዎን በመንገር የ ትርጉም አገልግሎት ያግኙ፡፡

  የውጭ ዜጎች የድንገተኛ ጊዜ ህክምና (ኤኤምአር) ሽፋን ብቁ የህክምና ድንገተኛ ሁኔታ ላጋጠማቸው እና የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን መስፈርቶችን የማያሟሉ ወይም ብቃት ያለው ግለሰብ ወይም የ 5-ዓመቱን ባር የማያሟላ ብቃት ያለው ፕሮግራም ነው፡፡

  የዋሽንግተን የስልክ መስመርን በ1-800-322-2588 በመደወል ማግኘት ያለብዎትን የተለያዩ የጤና ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን ለመለየት እና ለማመልከት ይረዳዎታል፡፡ ይህ የሚያጠቃልለው፡

  • (ሴቶች, ጨቅላ ልጆቸ & ልጆች የምግብ ፕሮግራም)
  • የህክምና ኢንሹራንስ ለልጆች, እርጉዝ ሴቶች እና አዋቂዎቸ
  • የእርግዝና መቆጣጠሪያ በቴክ ቻርጅ ፕሮግራም
  • የጤናና የቤተሰብ ቁጥጥር ክሊኒክ
  • የርግዝናና ህ ናት መገልገያ እቃዎች
  • የጡት ማጥባት አገልግሎተ
  • በተጨማሪም የምግብ አገልግሎት አላቸው፡፡
  የኢምግሬሽን እና ስደተኞች መረጃ

  Office of Immigrant and Refugee Affairs (OIRA) ስደተኞች ስለ COVID-19 እና ስለ ስደተኛ ስጋቶች አስፈላጊ እውነታዎችን እንዲረዱ ያግዛቸዋል

  • ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታን ከ ICE ጋር እንዲጋሩ አልተፈቀደላቸውም፡፡
  • ለኮቪድ-19 ምርመራ መደረግ እና ለበጎ አድራጎት ወይም ቅናሽ የሚደረግ የሕክምና እንክብካቤ ማግኘት ለአረንጓዴ ካርድ ወይም ለዜግነት ለማመልከት እድሎን አይጎዳውም፡፡
  • ለሥራ አጥነት ክፍያ ለማመልከት ትክክለኛ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ያስፈልግዎታል፡፡ የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ከአንድ ሰው ጋር መነጋገር ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 1-800-318-6022 ይደውሉ፡፡
  • የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን መቀበል በሕዝብ ቻርጅ ሕግጋት መሠረት አረንጓዴ ካርድዎን ወይም ዜግነትዎን አያሳጣም፡፡
  • በኮቪድ-19 የታመመውን ሰው ለመንከባከብ ወይም እራስዎን ለመንከባከብ የዋሽንግተን ስቴት ቤተሰብ ለማስታመም የሚከፈልበት እና የህክምና ፈቃድ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህንን ጥቅም ለማግኘት የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥር አያስፈልግዎትም፡፡ ESD የተለያየ አይነት ሰነዶች ይቀበላል፡
  • እርዳታ የሚፈልጉ የንግድ ባለቤት ከሆኑ፣ ከፌዴራል አነስተኛ ንግድ አስተዳደር (Federal Small Business Administration) ለአስቸኳይ ብድር ማመልከት የነዋሪ ካርድ ወይም ዜግነት የማግኘት ችሎታዎን አደጋ ላይ አይጥልም።

  The Office of Immigrant and Refugee Affairs (OIRA) ያለዎት ሁኔታ ወይም የቤተሰብ አባል ወይም የእርስዎ ጥቅሞችዎ ላይ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ የስደተኞች ጠበቃ፣ የኢሚግሬሽን ኦፊሰር ወይም በ Department of Justice (DOJ) እውቅና የተሰጠው ተወካይ እንዲያነጋግሩ ይመክራል። በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጠበቆች ማህበር (American Immigration Lawyers Association) በኩል ጠበቃ ማግኘት ይችሉ ይሆናል ወይም በ DOJ-እውቅና የተሰጠው የድርጅት ድርገፅን መጎብኘት ይችላሉ።

  OIRA ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ፕሮግራም አላቸው፡

  • የሰራ ፍለጋ እና ስልጠና፡፡
  • የኢሚግሬሽን ድጋፍ።
  • የወጣቶች ስልጠና፡፡
  • ለስደተኛ የእድሜ ባላጸጎች ፣ ለልጆች ፣ ለተማሪዎች እና ለሌሎች ድጋፍ ማድረግ፡፡፣
  • መደበኛ ፕሮግራሞች በ ኮቪድ-19 ወቅት በርቀት ክፍት ይሆናሉ። ጽ / ቤቱ ለስራ ወይም ለስራ አጥነት ለማመልከት ትምህርትዎን ለመደገፍ እና የመኖሪያ ቤት ድጋፍ ለመስጠት አዲስ አገልግሎቶች አሉት፡፡ የስደተኞች ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እና የስደተኞች የህክምና ድጋፍ ብቁነት እስከ ሴፕቴምበር 30 ቀን 2020 ድረስ ተራዝሟል።
  • ለአገልግሎቶች እና ለተጨማሪ መረጃ, በዚህ ስልክ 360-890-0691፡፡

  ስለ ስደተኛ መብቶች ጥያቄዎች ፣ በቁጥጥር ስር ላሉ ዘመዶች / ጓደኞች ድጋፍ ለማግኘት እና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎች ፣ማግኘት ይችላሉ የዋሺንግተን ስደተኞች አንድነት ኔትዎርክ የስልክ መስመር 1-844-724-3737፡፡ የ ስልክ ትርጉም አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፡፡

  የአእምሮ እና ስሜታዊ(Emotional) ጤና

  ይህ አስጨናቂ ጊዜ ሊሆን ይችላል። እርስዎ ወይም የምትወዳቸው ሰዎች ጭንቀት ፣ ኃዘን ፣ ፍርሃት ወይም ቁጣ መሰማት የ ተለመደ ነገር ነው፡፡ አንተ ብቻህን አይደለህም፡፡ እርዳታ መጠየቅ ምንም ችግር የለውም፡፡

  ለ ጭንቀት እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉም ሰው ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ ይለያያል፡፡ ማድረግ የሚችሉት በጣም አስፈላጊው ነገር እራስዎን ፣ ቤተሰብዎን እና ማህበረሰብዎን በተቻለ መጠን መንከባከብ ነው፡፡

  አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያት ለመቋቋም ምን ይረዳዎታል? ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር ተገናኝተዋል? ምናልባት በ ጥልቀት መተንፈስ እና ማፍታታት ፣ የተወሰነ የ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ጥሩ እንቅልፍ አግኝተዋል? ለራስ-እንክብካቤ ጊዜን ቅድሚያ መስጠት ውጥረትን ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል፡፡

  Washington Listensንን በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-833-681-0211፡፡ የ ስልክ ትርጉም አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፡፡ ለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ፣ ዋሽንግተን Washington Listens የተባለ የድጋፍ መርሐ ግብር ይፋ አደረገች፡፡ Washington Listens አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች ጭንቀትን ለመቆጣጠር እና በ ኮቪድ-19 የ ተነሳ ለውጦችን ለመቋቋም ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ Washington Listens በዋሽንግተን ውስጥ ላለ ማንኛውም ሰው የ ድጋፍ ባለሙያን ለማነጋገር ይገኛል፡፡ ደዋዮች በአካባቢያቸው ካሉ የማኅበረሰብ ሀብቶች ድጋፍ እና ግንኙነትን ይቀበላሉ። ፕሮግራሙ ምስጢራዊ ነው፡፡

  ችግር ከገጠምዎ እና ምክርን ለማግኘት ሰውን ማነጋገር ከፈለጉ ጥቂት አማራጮች አሉ፡፡

  • The Disaster Distress መስመር የስሜት መረበሽ ላጋጠማቸው ሰዎች አስቸኳይ የምክር አገልግሎት ይሰጣል ጭንቀት ከማንኛውም ተፈጥሮአዊ ወይም ከሰው ሰራሽ ጋር የተዛመደጭንቀት በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-800-985-5990፡፡ ምላሽ ሲያገኙ, ቋንቋዎን በመንገር የ ትርጉም አገልግሎት ያግኙ፡፡ የእገዛ መስመሩ በየቀኑ ለ 24 ሰዓታት ይገኛል፡፡
  • ቀውስ ግንኙነቶች በስሜት ቀውስ ውስጥ ላሉት ግለሰቦች ፣ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ፈጣን እርዳታ የሚሰጥ የ 24 ሰዓት ችግር መስመር አለው። በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ያገለግላል፡፡ የ ስልክ ትርጉም አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፡፡ በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-866-427-4747.
  • ብሔራዊ የራስን ሕይወት የመከላከል አነቃቂነት ራስን ስለ ማጥፋት ለሚያሰቡ ሰዎች የመከላከል እና የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል፡፡ የሚወዷቸውን ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን እና ጓደኞቻቸውን የሚረዱ መፍትሄ ለማግኘት የህይወት መስመሩን መደወል ይችላሉ። በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-800-273-8255. ይህ የስልክ መስመር በቀን ለ 24 ሰዓታት በሳምንት 7 ቀናት ይገኛል፡፡ ለነባር ወታደሮች የተወሰነ የእገዛ መስመር አለ፡፡ በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-800-273-8255 ወይም 1ን ይጫኑ. እርስዎ መስማት የተሳኖት እና የመስማት ችግር ካለብዎ, በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-800-799-4889.
  የምግብ ምንጮች

  18 ዓመት ወይም ከዚያ በታች የሆነ ልጅ ካለዎት ከት / ቤቶች ነፃ ምግብ ሊያገኙ ይችላሉ። በትምህርት ፕሮግራሞች ውስጥ የተመዘገቡ የአካል ጉዳተኞች አዋቂዎችም ለት / ቤት ምግብ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአብዛኛዎቹ አጋጣሚዎች እነዚህ ምግቦች እንደ አውቶቡስ ማቆሚያዎች ባሉ በትምህርት ቤት እና አቅራቢያ አካባቢዎች ይሰጣሉ። ነፃ ምግብ የሚሰጡ ከሆነ ለማወቅ የትምህርት ቤቱን ወረዳዎን ያነጋግሩ።

  ለነፍሰ ጡር ፣ ለአዳዲስ እናቶች እና ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት በጤና ጥበቃ ሴቶች ፣ ጨቅላዎችና ሕፃናት (WIC) ፕሮግራም በኩል ምግብ ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል፡፡ ለ ቋንቋ እርዳታ, በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-866-632-9992.

  በኮቪድ -19 ወቅት የምግብ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ የምግብ ባንኮች ሰዓታቸውን ሊቀይሩ ወይም እግረ መንገዳቸውን ለሚጠቀሙ ሰዎች ዝግ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከመሄድዎ በፊት እባክዎን ይደውሉ። Northwest Harvest የስቴት ደረጃ የምግብ ባንክ መረብ ነው። የከተማዎን ስም በ ድህረ ገጻችን ለማስገባት በስተ ግራ በሚገኘው አረንጓዴ ሳጥን ላይ ይተይቡ፡፡

  በምስራቅ ዋሽንግተን የሚኖሩ ከሆነ የምግብ ባንኮች ዝርዝር በ Second Harvest ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በአከባቢዎ ያሉ የምግብ ባንኮችን ዝርዝር ለማግኘት ካውንቲዎን በዚህ ድህረ ገጽ ይምረጡ፡፡

  መሰረታዊ የምግብ ጥቅማጥቅም ካርዶች

  መሰረታዊ የምግብ ጥቅማጥቅም (EBT) ካርዶች ምግብ ለመግዛት ይጠቅማሉ እና ለብዙ ሰዎች ማግኘት የሚቻሉ ናቸው። የU.S. ዜጎች በዋሺንግተን ግዛት Department of Social and Health Services (DSHS) ድረገጽ ላይ መሰረታዊ ምግብ ገጽ የሚለው ላይ ለዚህ ጥቅማጥቅም ማመልከት ይችላሉ።

  ማስታወሻ: የፌደራል መንግስት ለተወሰኑ አዋቂዎች የሚሰራውን የስራ መስፈርት በዚህ ችግር ወቅት አግዶታል። ቢሆንም ግን፣ ለዚህ ጥቅማጥቅም ብቁ ለመሆን የፌደራል መንግስት የU.S. ዜጋ መሆንዎን ይጠይቃል።

  ከላይ እንደተገለጹት አይነት የዴቢት-ስታይል ካርዶች ሌሎች የፕሮግራም መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ብዙ ዜጋ ላልሆኑ ሰዎች ይገኛል። ለዚህ ጥቅማጥቅም በDSHS የመንግስት የምግብ ድጋፍ ፕሮግራም ላይ ማመልከት ይችላሉ (በእንግሊዘኛ ብቻ)።

  መረጃ ለቤተሰቦች

  ይህ ለመላው ቤተሰብዎ አስጨናቂ ጊዜ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ከልጆችዎ ጋር እንዴት ማስተካከል እንዳለቦት አንዳንድ ምክሮች እዚህ ያገኛሉ፡፡

  የ ቤተሰብ ውይይቶችን በምቹ ቦታዎች ያድርጉ እና የ ቤተሰብ አባሎች ጥያቄ እንዲጠይቁ አበረታታቸው፡፡ የሚረዱትን ቋንቋ ለመጠቀም እና ልዩ ፍርሃታቸውን ወይም የተሳሳቱ አመለካከቶቻቸውን ለመፍታት ከትናንሽ ልጆች ጋር የተለየ ውይይት ለማድረግ ያስቡበት።

  ምንም እንኳን መረጃዎን ማወቅ ቢያስፈልግዎትም ፍርሃትን ወይም ሽብርን ሊያሳድጉ ለሚችሉ ሚዲያዎች ወይም ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጋላጭነትን ያቀንሱ፡፡ ልጆችዎ በሚዲያ ስለ ወረርሽኙ ተጋላጭነታቸው ምን ያህል ጊዜያቸው በማህበራዊ ድህረ ገጾች ወይም ሚዲያዎሽ እንደሚያሳልፈ ይቆጣጠሩ(ይገድቡ)፡፡

  ጥያቄዎችን በማበረታታት እና አሁን ያለውን ሁኔታ እንዲገነዘቡ በማድረግ ልጆችን በመርዳት ላይ ያተኩሩ፡፡

  • ስሜቶቻቸውን እንዲገልጹ ያድርጓቸው እናም ሃሳባቸውን ይቀበሏቸው።
  • በስዕል ወይም በሌሎች እንቅስቃሴዎች ስሜታቸውን እንዲገልጹ ያግዙዋቸው፡፡
  • ቫይረሱ እንዴት እንደሚሰራጭ እና እያንዳንዱ የመተንፈሻ አካላት የሚያጠቃ በሽታ ኮቪድ-19ን ሊያስከትለው የሚችል ኖቬል ኮሮና ቫይረስ አለመሆኑን በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ ወይም የተሳሳተ ግንዛቤን ያብራሩ።
  • ምቾት እና ተጨማሪ ትዕግስት ያዳብሩ።
  • በመደበኛነት ወይም ሁኔታው ሲቀየር ከልጆችዎ ጋር እንደገና መገናኘትዎን ያረጋግጡ።
  • የመኝታ ጊዜያት ፣ ምግብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜ ሲወስድ የቤተሰብዎን ፕሮግራም ወጥነት ይያዙ፡፡፣ እንደ ንባብ ፣ ፊልሞችን ማየት ፣ ሙዚቃ ማዳመጥ ፣ ጨዋታ መጫወትን ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ላይ መሳተፍ ወይም በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍን (መፀለይ ፣ በአገልግሎት ላይ መሳተፍ) እና እርስዎ እና ቤተሰብዎ በሌሎች አስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ የተሻሉ እንዲሆኑ ያደረጓቸውን ነገሮች በቤትዎ ለማድረግ ጊዜ ይስሩ፡፡
  • እንደ ብቸኝነት ፣ ድብርት ፣ በሽታ ሊያመጣ ይችላል የሚል ፍርሃት ፣ ጭንቀት ፣ ውጥረት እና ሽብር ያሉ ስሜቶች እንደ ወረርሽኝ ላሉ አሳሳቢ ሁኔታዎች የተለመዱ ምላሾች ናቸው፡፡
  • ከቤተሰብዎ እና ከባህላዊ እሴቶችዎ ጋር በሚጣጣሙ አስደሳች እና ትርጉም ያለው እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ ቤተሰብዎ ያግዙ፡፡
  ተጨማሪ ማጣቀሻ እና መረጃዎች

  Washington State Commission on Asian Pacific American Affairs (CAPAA)