ለመሰብሰብ መመሪያ

Image

እኛ የምናውቀው እነሆ: እኛ የምናውቀው እነሆ: አብረውን ከማይኖሩ ሰዎች ጋር መሰብሰብ—ጓደኞችን እና ቤተሰቦችም ቢሆኑም—COVID-19 ሊያዛምት ይችላል። በስብሰባው ላይ ብዙ ሰዎች በተገናኙ እና ይህ ግንኙነት ብዙ ሰዓት በቆየ ቁጥር፣ በበሽታው የመያዝ እድል ከፍ እያለ ይሄዳል።

ምንም እንኳን COVID-19 ክትባት አሁን ማግኘት የሚቻል ቢሆንም በስቴታችን ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው ክትባቱን እስከሚያገኝ ድረስ ወራት ይወስዳል። ጭምብል ማድረጋችንን መቀጠል፣ በ6 ጫማ (2 ሜትር) ርቀታችንን መጠበቅ እና አብረናቸው ከማንኖር ሰዎች ጋር መሰብሰብን ማስወገድ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ አሁን አስፈላጊ ነው።

በ COVID ወቅት የበዓል አከባበሮች

በአል አከባበሮቻችን በወረርሽኙ ወቅት የተለዩ መሆን አለባቸው። እና ያ ከባድ ነው። ነገር ግን ምንም እንኳን ብንለያይም ትንሽም ቢሆን የበለጠ አብሮ ለመሆን ብዙ መንገዶች አሉ።

በስክሪን ላይ መሰብሰብ | በእርግጥ ይህ ተመሳሳይ ላይሆን ቢችልም የተወሰኑ የቨርችዋል የበዓላት ስብሰባዎችን ማዘጋጀት ከመለያየት የሚመጣውን ጫና ሊያስወግድ ይችላል። በመስመር ላይ በመሰብሰብ ምግብ ማብሰል፣ ቡና ወይም ሻይ አብሮ መጠጣት፣ የእጅ ሥራ ፕሮጀክት መስራት፣ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ወይም ታሪኮችን ማንበብ ትንሽም ቢሆን የምንናፍቀውን አብሮነት ሊፈጥር ይችላል። መርሃግብር በሚያስይዙበት ጊዜ የጊዜ ቀጠናዎችን ያስቡ፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ እውቀት የሌላቸው ሰዎች እንዲካተቱ ቀድመው እርዳታ ማግኘታቸውን ያረጋግጡ።

አድናቆት ማሳየት | በእንደዚህ ዓይነት ፈታኝ ጊዜ ውስጥአንድ ሰው፣ የቤት እንስሳ፣ ቦታም ሆነ እቃ የምናመሰግንባቸውን ነገሮች ቆም ብሎ ማሰብ ጥሩ ስሜት ሊኖረው ይችላል። በእነዚህ ለምን አመስጋኞች እንደሆኑ ለመግለጽ፣ እነዚህን ብሩህ ነጥቦች በመጻፍ ወይም ማስታወሻዎችን፣ ጽሑፎችን ወይም ኢሜይሎችን ለሚቀርቧቸው ሰዎች በመላክ ያድምቋቸው።

የርቀት የምግብ መዋጮ | አብረው ከመሰብሰብ ይልቅ፣ ለጓደኞች እና ለቤተሰብ ምግብ ማዘጋጀት እና እርስ በእርስ ወደ ቤታቸው ማድረስ ይችላሉ። ወይም ለአንድ ምግብ ወይም ምሳ ለመስራት የሚውል ንጥረ ነገሮችን ብቻ ያቅርቡ። ከዚያ ለማብሰል ወይም ለመምገብ ወደሚወዱት የቪዲዮ ውይይት መተግበሪያ ይግቡ።

አንድ ላይ የምግብ አዘገጃጀትንይማሩ | አንድ ተወዳጅ የቤተሰብ የምግብ አዘገጃጀት ይምረጡ፣ ከጓደኞችዎ ወይም ከቤተሰብዎ ጋር ቀደም ብለው አንድ የምግብ ንጥረ ነገር ዝርዝር ያጋሩ፣ ከዚያ በቨርችዋል አንድላይ በመሰብሰብ ለማብሰል ወይም ለመጋገር ይሞክሩ።

የጨዋታ ምሽት | ውድድር የሚያስደስትዎ ከሆነ፣ የቨርችዋል ስብሰባዎን ከውይይት በዘለለ ውድድር ያድርጉት። ጨዋታዎችን ይጫወቱ፣ የቨርችዋል የምግብ-ውድድር፣ የችሎታ ውድድር፣ ወይም ቡድኖች የተለመዱ እና ያልተለመዱ እቃዎች በቤት ውስጥ የሚፈልጉበት የተደበቀ ፍለጋ ጨዋታ ያሉ ይሞክሩ።

የመሰብሰብ ደህንነት ማረጋገጫ ዝርዝር

በጣም ደህንነቱ የተጠበቀው ምርጫ አብረው ከማይኖሩባቸው ሰዎች ጋር በአካል መሰብሰብን ማስወገድ ነው። ያንን ምርጫ በማድረግ፣ የ COVID-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር ይረዳሉ። ከቤተሰብዎ ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር ለመሰብሰብ ከወሰኑ፣ የ COVID-19 በሽታን የማሰራጨት አደጋ ሁልጊዜ አለ። ከዚህ በታች ያሉት ምክሮች ያንን አደጋ ለመቀነስ የሚረዱ ቢሆንም አሁንም አደጋ አለ።

እና ያስታውሱ፣ ከመሰብሰብዎ በፊት፣ በአካባቢዎ ያለውን የገደብ መስፈርቶች ያረጋግጡ  (ድረገጽ በእንግሊዘኛ).

ከመሰብሰብዎ በፊት

 • ቀድመው ያቅዱ። በጣም አስተማማኙ አማራጭ አብረዋቸው ከማይኖር ከማንም ጋር በቨርችዋል መሰብሰብ ነው። በአካል ለመሰብሰብ ከወሰኑ፣ አብረው ጊዜ በሚያሳልፉበት ወቅት ለደህንነትን እንዴት ቅድሚያ እንደሚሰጡ ከጓደኞች (እና ከቤተሰብ) ጋር በትክክል ግልፅ ያድርጉ። ሁሉም ሰው ምን መጠበቅ እንዳለበት እንዲያውቅ የሚረዱ የተወሰኑ መሰረታዊ ደንቦችን ያዘጋጁ።
 • የእንግዳ ዝርዝርዎን ይከልሱ።
  • በመጀመሪያ ደረጃ፣ ትንሽ ያድርጉት – አብረዋቸው ከማይኖሩ ከአምስት ሰዎች በታች። እያንዳንዱ ሰው ስድስት ጫማ ተራርቆ የሚቆይበት ቦታ መያዙን ያረጋግጡ።
  • በመቀጠል፣ ማንን እንየጋበዙ እንደሆነ ያስቡ። ከተጋበዙት ውስጥበ ከፍተኛ አደጋ ምድብውስጥ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችወይም ልጆች አሉ? እንደ እቅድዎ አካል ልዩ ፍላጎቶችን እና የጥንቃቄ እርምጃዎችን ያስቡ። ያስታውሱ፣ በ COVID-19 የተነሳ በከባድ ሁኔታ ሊታመሙ የሚችሉ ሰዎችን ላለመጋበዝ መወሰን የእንክብካቤ ተግባር ነው። በቨርችዋል ለመገናኘት ሌሎች መንገዶችን ይፈልጉ።
 • ፈጣሪ ይሁኑ። ምግብ ማጋራት የማያካትቱ አስተማማኝ የመሰብሰብ መንገዶችን ያስቡ። ሰብሰብ ብለው በእግር ለመጓዝ ወይም ሌሎች ከቤት ውጪ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይገናኙ—ስድስት ጫማ (2ሜ) ርቆ መቆየትን ያስታውሱ።
 • ይራራቁ ይበሉ። ሁሉም ሰው ሁልጊዜ ስድስት ጫማ (2ሜ) ርቆ እንዲቆይ መቀመጫዎችን ያዘጋጁ። በመመገቢያ ጠረጴዛ ዙሪያ ከመሰብሰብ ይቆጠቡ።
 • ትንሽ ያድርጉት። አብረዋቸው የማይኖሩት የእንግዶቹን ብዛት ወደ አምስት ወይም ከዚያ በታች ይገድቡ። ቦታዎ እያንዳንዱ ሰው ስድስት ጫማ (2ሜ) ተራርቆ እንዲቆይ የሚያስችል መሆኑን ያረጋግጡ።
 • አጭር ያድርጉት። ስብሰባው ከሁለት ሰዓታት በታች ይሁን። አጭር ጊዜዎች COVID-19 የመሰራጨት እድሉን አነስተኛ ያደርገዋለል እናም አንድ ሰው የመጸዳጃ ክፍልን የመጠቀም እድሉ አነስተኛ ይሆናል። አጭር ስብሰባዎች እጆች እና ንጣፎች በአግባቡ በንጽህና መያዛቸውን ቀላል ያደርጋሉ።
 • የጤና ምርመራ ያድርጉ። ባለፉት 2 ሳምንታት ውስጥ እንደ ሳል፣ ትኩሳት ወይም የትንፋሽ እጥረት ያሉ ምልክቶች ያሉበት ሰው መኖሩን ይጠይቁ። እንግዶች ከመድረሳቸው በፊት ሙቀታቸውን እንዲፈትሹ ይጠይቋቸው። ትኩሳት ያለበት— ወይም ሌሎች ምልክቶች ያሉበት ወይም ባለፉት 2 ሳምንታት ውስጥ በ COVID-19 ከተያዘ ሰው ጋር እንደተገናኘ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው—ቤት ውስጥ መቆየት አለበት።
 • ልጆችን ይስቡ። ልጆች በስድስት ጫማ ርቀት ላይ ለመጫወት ይቸገራሉ፣ ስለዚህ ጭምብል ማድረግ እና አሻንጉሊቶችን ወይም ምግብን አለመጋራት በጣም አስተማማኙ የድርጊት እቅድ ሊሆን ይችላል። ያስታውሱ: ከ 2 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች በጭራሽ ጭምብል ማድረግ የለባቸውም!
 • የምግብ እቅድ ያዘጋጁ። በጣም ደህንነቱ የተጠበቀ አማራጭ የሚሆነው መሰብሰብዎን በምግብ መካከል ለማድረግ ማቀድ ነው። ምግብ የሚያቀርቡ ከሆነ፣ ቀደም ብለው ምግብን በተናጠል ማቅረቢያ ላይ ያድርጉ እና የጋራ የሆኑ ሰሃኖችና እቃዎች ከማቅረብ ይቆጠቡ።
 • ይመርመሩ። ኔጌቲቭ መሆንዎን ለማረጋገጥ የ COVID-19 ምርመራ ያድርጉ። የምርመራዎን ውጤቶችዎን ለመቀበል ጥቂት ቀናት ሊወስድ የሚችል ሲሆን በሚጠብቁበት ጊዜ በቤት ውስጥ ራስዎን ለይተው ማቆየት አለብዎት። የምርመራ ውጤትዎ ኔጌቲቭ ከሆነ፣ ከተሰበሰበው ጋር በሚቀላቀሉበት ጊዜ አሁንም ጭምብል ማድረግ እና ከሌሎች ጋር ርቀትን ጠብቆ መቆየት ያስፈልግዎታል።
 • በቤት ውስጥ ያሉ ማህበራዊ ስብሰባዎች መስፈርቶች በቤትዎ ውስጥ እንግዳ የሚኖርዎት ከሆነ፣ በአካባቢው ያለውን ለይቶ የማቆየት መስፈርት ማሟላት አለባቸው (ድረገጽ በእንግሊዘኛ)። ይህ ከቤት ውጭ ለሚደረጉ ስብሰባዎችም ጥሩ ሀሳብ ነው።

በሚሰበስቡበት ጊዜ

 • ቀድመው እና በተደጋጋሚ ይታጠቡ። ንጹህ እጆች። የእጅ መታጠቢያ ገንዳ ከሌለ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ያቅርቡ።
 • ጭምብል ያድርጉ። በማንኛውም ጊዜ የ ፊትመሸፈኛ ይልበሱ። ሰዎች ከረሱ ተጨማሪ ጭምብሎችን ያዘጋጁ።
  • ልጆች እና ጭምብሎች። ከ 2 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች በጭራሽ ጭምብል ማድረግ የለባቸውም። ከቤተሰቦቻቸው ውጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር ሲሆኑ፣ ከ 2 እስከ 4 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ልጆች በአዋቂዎች ቁጥጥር የፊት መሸፈኛዎችን መልበስ አለባቸው፣ እና ዕድሜያቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ልጆች የፊት መሸፈኛ እንዲለብሱ ይጠየቃሉ። (ቀደም ሲል ነባር የጤና ችግር ያለበት ልጅ ካለዎት እና ስለ ጭምብል አሳሳቢ ነገሮች ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ።)
 • ማጋራት የለም። የምግብ መወዋጨጮዎች፣ ቡፌዎችን ወይም ሌሎች የተጋራ ምግብን ያስቀሩ። እንግዶች የራሳቸውን ኩባያ፣ ሳህኖች እና ዕቃዎች እንዲያመጡ ይጠይቋቸው። ወይም፣ በተሻለ መልኩ፣ ትንሽ ስብሰባዎን በምግብ መካከል ለማድረግ ያቅዱ። እና ያስታውሱ፣ መጫወቻዎችን ወይም ሌሎች ነገሮችን አይጋሩ፣ እና የሚጋሩት ንጣፎችን ከመጠቀም ይቆጠቡ።
 • ያጽዱ፣ ያጽዱ፣ ያጽዱ። ከመሰብሰብ በፊት፣ በሚሰበሰብበት ጊዜ እና በኋላ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉ ንጣፎችን በፀረ-ተባይ ያጽዱ።
 • የቅርብ ንክኪዎችን ከማድረግ ይቆጠቡ። አብረዋቸው ከማይኖሩ ሰዎች ጋር ሲሆኑ ፈገግታዎች እና የአየር ላይ እቅፍ ብቻ ያሳዩ የስድስት ጫማ ርቀት ደንብ ከቤተሰብዎ ውጭ ላሉ ሕፃናትም ይሠራል። በድጋሚ፣ ፈገግታዎች እና የአየር ላይ እቅፍ ብቻ እና መጫወቻዎችን ወይም መክሰስን መጋራት የለም። ይህ ከባድ ነው፣ ግን ልጆችን—እና አያቶችን—አስቀድመው ያዘጋጁ።
 • መስኮቶችን ይክፈቱ። እንግዶችዎ ለቤት ውስጥ መሰብሰብ ገደቦች ሁሉንም መስፈርቶች ካሟሉ እና እርስዎ የቤት ውስጥ ስብሰባ እንዲኖርዎት ከወሰኑ፣ ትክክለኛ የአየር ዝውውር እንዲኖር ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው ክፍሎች ውስጥ መስኮቶችን ክፍት ያድርጉ። እንግዶች ሞቅ ያለ አለባበስ እንዲለብሱ ይጠይቁ!

ከተሰበሰቡ በኋላ

 • እጅዎን ይታጠቡ (እንደገና)። ለ 20 ሰከንዶች በሳሙና እና ውሃ ይታጠቡ።
 • ሳኒታይዘር ይጠቀሙ። ንጣፎችን ሁሉ እነዚህም እንግዶች ሊነኳቸው የሚችሉትን እንደ የጠረጴዛ ወለሎች፣ ባንኮኒዎች፣ የበር እጀታዎች እና የመታጠቢያ ክፍል መሣሪያዎችን በሳሙና እና በውሃ ያጽዱ ከዛዛ በጸረ-ተባይ ያጽዱ።
 • ምልክቶችን ይከታተሉ። በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት ውስጥ ፖዚቲቭ የሆነ ምርመራ ከተገኘ ለነበሩት ሰዎች ሁሉ ያሳውቁ። ከተጋለጡ ምን ማድረግ እንዳለብዎየበለጠ ይረዱ ።

እየተቸገረ ያለ ሰው የሚያውቁ ከሆነ...

ይድረሱለት። ከጎኑ እንደሆኑ ያረጋግጡለት። አካላዊ ርቀትን በሚጠብቁበት ጊዜ እንዴት ድጋፍን ማሳየት እንደሚቻል የሚጠቁሙ አንዳንድ ሀሳቦች፡

 • ተመዝግበው ለመግባት ወይም ለቪዲዮ ውይይት መደበኛ ቀን ወይም ሰዓት ያመቻቹ
 • የማበረታቻ እና የፍቅር ቃላትን የያዘ ደብዳቤ በፖስታ ይላኩላቸው
 • በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መስተንግዶ፣ ከሚወዱት ምግብ ቤት ወይም ከሚወዱት መጽሐፍ ይላኩ
 • ሳይፈርዱ ያዳምጡ።
 • በዚህ ወቅት የሀዘን፣ የጭንቀት እና የብቸኝነት ስሜት መሰማት የተለመደ መሆኑን እና ይህ ደግሞ ለዘለአለም እንዳልሆነ ያረጋግጡላቸው። እንዲሁም፣ ቢፈልጉ እርዳታ እንዳለ ያረጋግጡላቸው።
 • የሚቻል ከሆነ ሁለታችሁም ለመመርመር ተዘጋጁ፣ ከዚያ ለሁለት ሳምንታት ራስችሁን አግልሉ። ከዚያም እነሱ በዚህ አመት ጊዜ ሊፈልጉት የሚችለውን ድጋፍ እና ምቾት ለመስጠት የረጅም ጉብኝትን ማቀድ ይችላሉ።

በ COVID-19 ምክንያት ጭንቀት እያጋጠመዎት ከሆነ፣ ለድጋፍ እና ለግብዓት በ 833-681-0211 ወደ Washington Listens መስመር ይደውሉ። ነፃ የቋንቋ ድጋፍ ይገኛል። ለ Washington Relay አገልግሎት 711 ይደውሉ።